በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ዑመር ሁሴን(ዶ/ር) ከፔፕሲኮ ኩባንያ የአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና ደቡብ እስያ የኮርፖሬት ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት Mr. Wael Ismail ጋር ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ውይይት አድርገዋል፡፡
ፔፕሲኮ የአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና ደቡብ እስያ ክልሎችን ያቀፈ ሲሆን፣ በርካታ መሪ አለምአቀፍ የምግብ እና መጠጥ ብራንዶችን በማምረት በአለም አቀፍ ገበያዎች እንደ ሚያሰራጭ በመግለጽ፣ በምስራቅ አፍሪካ ለምርቶቻቸው ከፍተኛ የገበያ እድሎች መኖሩን አብራርተዋል።
በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ አቅም እና ልምድ እንዳላት ጠቁመው፣ ኢትዮጵያ ሄደው በግብርና የስራ መስክ ለመሰማራት ፍላጎታቸውን በማሳየት፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ አገራችን ሄደው የቅድመ-ኢንቨስትመንት ጉብኝት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
ክቡር አምባሳደር በበኩላቸው አገራችን በግብርና መስክ መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች ወደ ስራ እንዲገቡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚኒሽን እና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ግብርና ሚኒስቴር ተቋማት በጋራ ለባለሀብቱ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ እና እድል ማብራሪያ እንደሚሰጡ በመግለጽ፣ በቀጣይ ወደ አገር ቤት ለመሄድ ሲያስቡ ከሚመለከታቸው መ/ቤቶች ጋር ተገናኝተው ውይይት እንዲያደርጉ መድረክ እንደሚመቻችላቸው መግባባት ላይ ተደርሷል።